Abstract:
የዓለም ጤና ድርጅት የኖቭል ኮሮና ቫይረስ በሽታ ከታሕሳስ 21, 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በቻይና ዉሃን (Wuhan) ክልል
የተከሰተ መሆኑን አሳወቋል፡፡ ይህ ቫይረስ ቀደም ብሎ የሚታወቅ በሽታ አምጭ ተኅዋስ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት የተከሰተው
ግን አዲስ የቫይረስ ዓይነት እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን እስከ ዛሬ ማለትም ጥር 15, 2012 ዓ.ም. ድረስ በጠቅላላ አምስት መቶ
ሰማንያ አንድ (581) ታማሚዎች ሪፖርት ተደርጓል፡፡ አምስት መቶ ሰባ አንድ (571) የሚሆኑት ታማሚዎች ከቻይና ብቻ
ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን ከነዚህም ታማሚዎች ውስጥ 17 የሚሆነት ህይወታቸው አልፏል፡፡ በቻይና በመጀመሪያ የበሽታው
ምልክት የታየው በውሃን ከተማ በሚገኝ የባሕር ምግብ ገበያ የባሕር ምግቦችን የሚያዘጋጁና የሚያቀርቡ ሰዎች ላይ ሲሆን
በሽታው ወደ አሜሪካ፣ ጃፓን፣ ታይላንድ፣ ኮሪያ ሪፐብሊክ እና ሲንጋፖር ከቻይና በተነሱ ተጓዦች አማካኝነት መስራጨቱ
ታውቋል፡፡