Abstract:
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጥራታቸዉ የተረጋገጠ መሰራታዊ መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋና ቀጣይነት ባለዉ መልኩ
ለመንግስታዊ የጤና ተቋማት ለማቅረብ በአዋጅ ቁጥር 553/99 የተሰጠው ተልዕኮ ነው፡፡ ይኸንን ተልዕኮ እዉን ከማድረግ አንጻር
አገልግሎቱ የተለያዩ የስራ ክፍሎችን በማደራጀት እና አሰራሮችን በመዘርጋት እየተገበረ ይገኛል፡፡ ለዚህም በአገልግሎቱ የመድኃኒትና
የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች መጋዘን አያያዝና ክምችት አስተዳደር በዋናው መ/ቤትና በቅርንጫፎች ውስጥ ቀልጣፋ፣ግልጽና ተጠያቂነት
የሰፈነበት አሰራር ለመዘርጋትና ወቅቱን ያገናዘበ መመሪያ መዘጋጀቱ የሚያበረክተዉ አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ነዉ፡፡