Abstract:
ምንም እንኳ ኢትዮጵያ የጤና እንክብካቤ እና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ተጨባጭ በሆነ
መልኩ ያሻሻለች ቢሆንም አሁንም ግን ብዙ መስተካከል ያለባቸው ክፍተቶች እና ተግዳሮቶች
ይታያሉ፡፡ በጤና ዘርፉ ያሉ ላቦራቶሪዎች፣ ብሔራዊ የሪፈረንስ ላቦራቶሪን ጨምሮ በአብዛኛው
አመቺ ባልሆነ የመሰረተ ልማት፣ ደካማ የስራ ደህንነቱ ባልተጠበቀ አከባቢ፣ የመሳሪዎች እጥረት፣
የግብዐቶች መቋረጥ እና የላቦራቶሪ ጥራት መለኪያ ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡